የስኳር በሽታ ሁልጊዜ ምልክት ላያሳይ ይችላል። ከስኳር በሽታ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ከ40% በላይ የሚሆኑት በሽታው እንዳለባቸው ያልታወቀ ሲሆኑ በዚህም ምክንያት የሚያስፈልጋቸውን ርዳታ ላያገኙ ይችላሉ።
ማወቅ ያለብን እውነታዎች
🌍 ከስኳር በሽታ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ከ4 እጥፍ በላይ ጨምሯል፤
በ1990 ከነበረበት 200 ሚሊዮን በ2022 ወደ 830 ሚሊዮን አድጓል።
💊 በ2022 ከስኳር በሽታ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ለበሽታቸው መድኃኒት አይወሰዱም።
⚠️ የስኳር በሽታ ለከፋ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል ዓይነ ስውርነት፣ የኩላሊት መድከም፣ የልብ ድካም፣ ስትሮክ እና የታችኛው የሰውነት ክፍል (እግር) መቆረጥ ይገኙበታል።
🧒 የስኳር በሽታ ካለባቸው ሰዎች መካከል ከ95% በላይ የሚሆኑት ዓይነት 2 (Type 2) የስኳር በሽታ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህም በአሁኑ ጊዜ በልጆች ላይ በተደጋጋሚ እየታየ ነው።
የስኳር በሽታ ምልክቶች
- ከፍተኛ የውኃ ጥም
- ቶሎ ቶሎ መሽናት
- የእይታ መደብዘዝ
- የድካም ስሜት
- ያለ ምክንያት ክብደት መቀነስ
💡 በዓይነት 2 የስኳር በሽታ ወቅት ምልክቶቹ ቀላል ሊሆኑ ስለሚችሉ እስኪታወቁ ድረስ ብዙ ዓመታትን ሊወስዱ ይችላሉ።
ዓይነት 2 የስኳር በሽታን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች
🏃 በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ ያህል መካከለኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ንቁ ይሁኑ
🥗 ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ፤ ስኳር እና የረጋ ስብ (saturated fat) ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ
⚖️ ጤናማ የሰውነት ክብደት መኖር
🚭 ትምባሆ አያጭሱ
❤️🩹 የስኳር በሽታን ቀድሞ ለማወቅ ከሁሉ የተሻለው መንገድ በጤና ባለሙያ መደበኛ የጤና ምርመራ እና የደም ምርመራ ማድረግ ነው።
🔗 የበለጠ ለማወቅ፡ bit.ly/3Va0rgL



